በፌስቡክ ላይ በፌዝ እና በአሽሙር መልክ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች
በማኅበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃን በስፋት እንዲሰራጪ ምክንያት ከሚሆኑ ዋነኛ መንገዶች መካከል በተሳሳተ ስምና አካውንት የሚሰራጭበት መንገድ ሲሆን ሌላው ደግሞ በቀልድ መልክ የሚሰራጩ መረጃዎች ናቸው፡፡ በተለይ አሁን ላይ በቀልድ መልክ መሀሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት የሚፈጥራቸው አደጋዎች መጠን ከፍ እያለ መጥቷል፡፡ ለዚህ ጹሑፍ እንደማሳያ በፌስቡክ መለያ (እካውንት ) ጌታቸው አሰፋ የሚል አካውንት መርጠናል፡፡ ይህ መለያ ከ 93,000 በላይ ተከታዮች ይዞ ይገኛል። ይዘቶቹ በተለይ በፖለቲካ ቀልድ( Satire and Parody ) ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ነገር ግን በአንዳንድ ልጥፎቹ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን እና የፖለቲካ ክስተቶችን በቀልድ መልክ በማድረግ የተሳሳተ መረጃ ለተከታዮቹ እያሰተላለፈ ይገኛል።
ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ ምሳሌዎችን ጠቅሰን እንመለከታለን
ምሳሌ 1

ጹሁፉ በፈረንጆቹ ነሐሴ 22፤ 2025 ዓ.ም ነው የተለቀቀው፡፡ በዚህ ልጥፍ ላይም ‹‹የአሸንዳ በዓል በትግራይ ደቡባዊ ዞን ላሊበላ ከተማ እየተከበረ ነው›› በሚል ለቀልድ በሚመስል መልኩ የተሳሳተ መረጃን አሰራጭቷል። ሆኖም ይህ ፖስት ከላይ እንደተጠቀሰው ሳይሆን ትክክለኛ መረጃውና ዜናው ትክክለኛ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ላይ ይገኛል። በዚህ ዘገባ ላይም ‹‹ በአማራ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች ሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው ›› በሚል ተዘግቧል፡፡ ይህም በዚህ ሀሰተኛ ገጽ ‹‹በትግራይ ደቡባዊ ዞን ላሊበላ ከተማ›› የሚል ትክክል ያልሆነ ቦታን ተጠቅሟል፡፡ ይህ ልጥፍ ከ2.3 ሺ በላይ የተለያዩ ሪአክሽኖች፤ ከ600 በላይ አስተያየትና ከ65 በላይ ሼር አግኝቷል፡፡
ይህው ገጽ በሌላ ልጥፉ ‹‹አሸንዳ እና መሰል ስሞች የሚከበሩበት ቦታ በጠቅላላ የትግራይ ግዛት ነው›› በሚል ይገጻል ይህም ከላይ በቀልድ መልክ የሚያቀርባቸው መረጃዎች ይህንን ለማሳየት የሚጠቀምበት እንደሆነና የባህል ሽሚያ ለመፍጠር በታሰበ መልኩ 㝕ሚን ሽለመኆኑ ማሳያ ነው፡፡
ምሳሌ 2:

በዚሁ ገጽ በቄራ ጎርፍ እንደተከሰተ ተደርጎ የተሰራጨ ቪዲዮ 280 ሺህ እይታ ፣ 1,300 ሪያክሽን እና 45 መጋራቶች(share) ነበረው። በተጋራው ሃሰተኛ ቪዲዮ ላይም "ለሚችል ሰው ሰጥቶ መገላገል አይሻልም?" የሚል ፅሁፍ ሲኖር ከቪዲዮው ስርም "ቄራ ኮሪደር" የሚል ፅሁፍ አለ። ጹሑፋ ስላቅ ሲሆን መረጃውም ትክክል አልነበረም፡፡ በቪዲዮውን ለማጣራት በሰራነው ሥራ ይህ ቪዲዮ የተቀረጸው በቄራ ሳይሆን በዴትሮይት አየር ማረፊያ የተቀረጸ ነው፡፡
ቀልድ /ስላቅ (Satire and Parody) በግልጽ ካልተሰየሙ ( Label ) ተመልካቾችን ተከታዮችን ሊያሳስት ይችላል። ከላይ እንዳነሳነው ከሆነና እነዚህ ደግሞ በሀሰተኛ ገጾች የሚተላለፉ ከሆነ ጉዳቱን ይጨምረዋል፡፡ ሁል ጊዜ በፌስቡክ ያሉ ይዘቶችን ቀልድ ነው በሚል ለሌሎች ከማሰራጨታችን በፊት ሊዬደርስ ስለሚችለው ጉዳት ማሰብ አስፈላጊ ነው።
ፀሃፊ: ቃለአብ መልካሙ