ቶዮታ ያለ ባትሪ ወይም ቻርጅ በውሃ ኃይል ብቻ የሚንቀሳቀስ ሞተርን ለገበያ አቅርቧል በማለት የተሰራጨ ሃሰተኛ መረጃ
ሃሰተኛ መረጃው ምንድን ነው?

የተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ የዓለማችን ትልቁ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ሞተር ውሃን እንደ ነዳጅ የሚጠቀም እና የሊቲየም ባትሪዎችን ወይም ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እንደሚያስወግድያትታል። በተጨማሪም ዓለም አቀፉን የአውቶሞቢሎች ኢንዱስትሪ በሚያናውጥ እርምጃ ቶዮታ በኤሌክትሮላይዝስ አማካኝነት የሚፈጠረውን የውሃ ተንቀሳቃሽ ሞተርን በሃይድሮጅን የሚንቀሳቀስ የውሃ ትነት ብቻ ይፋ አድርጓል ይላል። ነገር ግን ቶዮታ ለ AFP Fact Check ዘገባው ውሸት መሆኑን ተናግሯል። ባለሙያዎችም ይህ ጽንሰ-ሐሳብ እጅግ በጣም ውጤታማ እና በተግባር ግንየማይሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሃሰት ዘገባው የተካተቱ ነገሮች
ፖስቱ የሁለት ፎቶግራፎች ኮላጅ የያዘ ሲሆን አንደኛው ሱፍ የለበሰ ሰው የውሃ ሞተር ሲያቀርብ እና ሌላኛው የቶዮታ ምርት ስም ያለው ሞተር ነው፡፡ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ፎቶ ተደራቢ ተደርጎ ይታያል። በተጨማሪም የተሰራጨው መረጃ ቻይና ከእንግዲህ በኤሌክትሪክ መኪናዎች ያላትን ተወዳዳሪነት ልታጣ እንደምትችል በመጠቆም የተሻለ ተአማኒነት ለማግኘትም የቻይናውን ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ምስል አካትቷል።
በዜሮ በካይ ጋዝ ልቀት ተሸከርካሪዎች ውድድር በተለይ በኤሌክትሪክ እና በሃይድሮጂን መኪኖች መካከል ውሃ አንድ ቀን ሊተካቸው ይችላል የሚለው ተስፋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያገረሸው ታዋቂ ሀሳብ ነው። ነገር ግን ይህ መላምት በጠንካራ ሳይንሳዊ ማስረጃዎች የተደገፈ ሆኖ አያውቅም፣ እናም ቶዮታ በውሃ የሚሰራ ሞተር እየሰራ ነው የሚለው መረጃ ውሸት ነው።

የሃይድሮጂን ተሽከርካሪዎች
ቶዮታ የውሃ ሞተርን "እንደሚያመርት" ምንም አይነት መረጃ ለህዝብ አላጋራም።። የቶዮታ ኮርፖሬሽን ተወካይ የሆኑት ዣን ኢቭ ጃልት ለኤኤፍፒ በላኩት ኢሜይል ላይ "የውሃ ሞተር" ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ምንም ነገር እያዳበሩ እንዳልሆነና እየተሰራጨ ያለውን ጥያቄ "ውሸት መረጃ" መሆኑን ጠቅሰዋል።
ውሃ የኃይል ምንጭ ሊሆን ቢችልም እንደ ነዳጅ ማለት ግን አይደለም፡፡ ውሃ የሚመረተው ሃይድሮጂን ሲቃጠል ሲሆን ውሃ በአንዳንድ ሁኔታዎች እንደ የኃይል ምንጭ ሆኖ ሊሠራ ይችላል ። በመሆኑም "ቶዮታ" በውሃ የሚሰራ ሞተር ይፋ አድርጓል የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ተረጋግጧል።
ተመሳሳይ አይነት ታሪኮች በሚገጥሙን ሰዓት
● መሰል ታሪኮች ተዓማኒ የሆኑ መደበኛ ሚዲያዎች የዜና ሽፋን የመስጠት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚያ ላይ ማረጋገጥ ተገቢ ይሆናል።
● የፎቶ እና የቪዲዮ ይዘቶችን በጥልቀት በመመልከት አጠራጣሪነታቸውን በመጠኑም ቢሆን መለየት ይቻላል። ስለዚህ ይህንን የምንለይበትን ክህሎት ለወደፊቱ ማዳበር ጠቃሚ ይሆናል።
ፀሃፊ: አንዷለም አዲሱ