post-thumb

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሰታደር ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል ያላቸውን ሚዲያዎች አሳሰበ።

በተለይም አዲስ አድማስ ጋዜጣ እና እሱን ዋቢ በማድረግ የተለያዩ ሚዲያዎች " ፌደራል መንግስት በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል ሲሉ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል " ሲሉ አሰራጭተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በሀሰት ይህን አሉ የተባለው ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም የኢትዮጵያ ኃላፊ አቢባትዩ ዌን በተወያዩበት ወቅት ነው።

" ያሰራጩት ዘገባ ፍፁም የተሳሳተ ነው "  ያለው አስተዳደሩ ፥ ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም የኢትዮጵያ ኃላፊ አቢባትዩ ዌን በተወያዩበት ወቅት እንዲህ ያለውን ነገር እንዳላሉ አሳውቋል።

ሀሰተኛ መረጃ ያሰራጩ ሚድያዎች ያሰራጩትን የተሳሳተ ዘገባ እንዲያርሙ በጥብቅ አሳስቧል።

ውይይቱን በተመለከተ መረጃ ያሰራጨው የትግራይ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " በፌዴራል በኩል ትግራይ መልሳ ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰራች ነው የሚል ስጋት አለ ግን ህዝብ እና ጊዜያዊ አስተዳደሩ በምንም መልኩ  ጦርነት እንዳይቀሰቀስ በትኩረት እየሰሩ ነው።   በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄዎች ባይመለሱም አሁንም ሰላም ለማፅናት የጦርነት ደባብ ለማስወገድ በልዩ  ጥንቃቄና ሃላፊነት እንሰራለን " ሲሉ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ መናገራቸውን ነው ያሰፈረው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ