" የተከሰተ አደጋ የለም " - ለማ መሠለ (ዶ/ር)
ዛሬ እሁድ ከጥዋት ጀምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች " በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሬት ናዳ በኮንታ ዞንና በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ተከስቶ አስር ሰዎች ሞተዋል " ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ውሸት እንደሆነ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ለማ መሠለ (ዶ/ር) " አደጋ እንደተከሰተና አስር ሰዎች እንደሞቱ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀላፊነት የጎደለውና ውሸት ነው " ብለዋል።
" መረጃዎችን ከትትክለኛ የመረጃ ምንጭ መቀበል ይገባልም " ሲሉ አሳስበዋል።
ወቅቱ ዝናብ ጫን ያለበት ስለሆነ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ አከባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ፥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የፌስቡክ ገጽ እንደሌለው ኖሮትም እንደማያውቅ በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ ይወዳል። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው የተለያዩ አካላት በቲህቫህ ኢትዮጵያ ስም ሀሰተኛ ገጽ በመክፈት ያልተገቡ መረጃዎችን እያሰራጩ ነው ፤ ስለሆነም ውድ ቤተሰቦቻችን በፌስቡክ ላይ በቲክቫህ ስም የሚሰራጩ መረጃዎች የኛ አይደሉም።
#TikvahEthiopiaFamily