post-thumb

የንጋት ሃይቅን በተመለከተ የተሰራጩ አሳሳች ዘገባዎች

ስለ ንጋት ሃይቅ የውሸት ወይም አሳሳች መረጃ በተለያዩ መለያዎች እና የሚዲያ ዓይነቶች ተሰራጭቷል።

የተሰራጩት የተሳሳቱ መረጃዎች ምንድን ናቸው?

የመጀመሪያው ንጋት ሀይቅ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ነው የሚል ሲሆን እንደ 'GazettePlusEnglish' ያሉ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይህንን አሰራጭተዋል። ሃይቁን የፈጠረው ግድብ የሚይዘው 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ  ውሃ ከጣና ሀይቅ 32 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ የሚበልጥ ቢሆንም ሰው ሰራሽ ሃይቁን የኢትዮጵያ “ትልቅ ሐይቅ” ብሎ መፈረጅ ትክክል አይደለም።

ሌላኛው ንጋት ሃይቅ ለአለም አቀፍ የውሃ ስፖርቶች ዝግጁ ነው የሚለው ዘገባ ነው።'GazettePlusEnglish'ይህንን ነገር ቢዘግብም ለእንደዚህ አይነት ዝግጅቶች ምንም መሠረተ ልማት የለም። የስፖርት ዝግጅቱን ማዘጋጀት እምቅ ችሎታ እንጂ አሁን ያለው ነባራዊ እውነታ አይደለም።

እንደ ኦንላይን ኢትዮጵያ ያሉ አንዳንድ ገፆች ንጋትን “የአፍሪካ ትልቁ የውሃ ፕሮጀክት” ብለው ይገልጹታል።ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ቢሆንም ንጋት የአፍሪካ ትልቁ የሰው ሰራሽ ሃይቅ አይደለም።በአፍሪካ ከሚገኙ ትልልቆቹ የሰው ሰራሽ ኃይቆች የቮልታ ሃይቅ እና የናስር ሃይቅ ይገኙበታል።

የማህበረሰቡ ግንዛቤና ግልፀኝነት

ይህ የተሳሳተ መረጃ ሁልጊዜ ከመጥፎ ዓላማዎች የሚመጣ ሳይሆን በብዙ አጋጣሚዎች ከብሔራዊ ኩራት የሚመነጭ ቢሆንም ያልተገቡ አመለካከቶችንም ሊፈጥር ይችላል።

 የተሳሳተው መረጃ ህዝቡ ስለ ቱሪዝም፣ ግብርና ወይም መዝናኛ የማይጨበጥ ተስፋ እንዲያዳብር ሊያደርግ ሲችል  አለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ስኬቶቿን በግነት የምታቀርብ እንድትመስላቸው ያደርጋል።

ይህንን ለመከላከል. ቴክኒካዊ አሃዞችን በቀላል እና ወጥነት ባለው ክፍል ማብራራት፣  እምቅ እና የአሁኑን እውነታ መለየት እና ህብረተሰቡ ከማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች ይልቅ በይፋዊ የመንግስት ወይም የሃይድሮሎጂ ምንጮች መረጃን እንዲያረጋግጥ ማበረታታት የተሳሳተ መረጃ ስርጭቱን ለመቀነስ ያግዛሉ።