post-thumb

አቶ ማሞ ምህረቱ ከስልጣን ተነስተው ወይስ ተባረው?

አቶ ማሞ ምህረቱ በጥር ወር 2015 በወቅቱ የባንኩ ገዢ የነበሩትን ይናገር ደሴ(/) ተክተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን እንዲመሩ የተሾሙ ሲሆን ባንኩን በኃላፊነት ከመረከባቸው በፊትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትን ጨምሮ የመንግስት ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንድ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ  ዋና ስራ አስፈፃሚ ነበሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (/) የፖሊሲ አማካሪ እና የሃገሪቱ የንግድ አማካሪ በመሆንም ያገለገሉት አቶ ማሞ ምህረቱ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ከተሾሙም በኋላ በሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረው የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን የወሰዱት እርምጃ ዋነኛው ነው። ከሰባት ዓመት አገልግሎት በኋላ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ሆነው ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም የመንግሥት  ኃላፊነትም ጭምር በገዛ ፈቃዳቸው ከስራ መልቀቃቸውን  በX ገጻቸው ማጋራታቸው ይታወሳል።

በመቀጠል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኦፊሻል ድረ-ገጻቸው ለአቶ ማሞ ምህረቱ ላበረከቱት አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከአንድ ቀንም በኋላ አቶ ማሞ ምህረቱ ይህንን መሰናበቻ የሚመስል ምስል በX ገጻቸው አጋርተዋል።

የአቶ ማሞ ምህረቱን ስንብት ተከትሎ የተሰራጩ መረጃዎች

 በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ አቶ ማሞ ምህረተ ከስራ የለቀቀው በራሱ ፈቃድ አይደለም የሚሉ ጽሁፎች ተሰራጭተዋል። ነሀሴ 28 2017 አቶ ጃዋር መሀመድ በx ፖስታቸው ላይ፣ “mamo: I resigned, Abiy: No, I fired you” የሚል ልጥፍ አጋርተዋል። አቶ ማሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኃላፊነቱ ተነሱ የተባሉበት ደብዳቤም ተሰራጭቷል።

የተሰራጨው ደብዳቤ

የተሰራጨው ደብዳቤ

 

  • ስለ ደብዳቤው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልወጣም። በተለምዶ መንግስት እንደዚህ አይነት ደብዳቤ ሲልክ ይፋዊ መግለጫ በጽህፈት ቤቱና በሚዲያዎች በኩል ይፋ ይሆን ነበር።
  • ስለ ደብዳቤው ለማወቅ  ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቢደወልም ምላሽ አልተገኘም። የደብዳቤውን ትክክለኛነት ያውቁ እንደሆነ ወይም ማረጋገጥ እንደሚችሉ ለመጠየቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን በአካል በመገኘት በተደረገው ሙከራ  ረጋገጥ አልተቻለም
  • ይህ የሚያሳየው ደብዳቤው እውነት ሊሆን ቢችልም ከመንግስት ያለ ኦፊሻል ማረጋገጫ ስለሌለ ሙሉ በሙሉ ሊታመን አይችልም። ግልጽ ማስረጃ ሳይኖር ይህን ደብዳቤ በፍጥነት ላለማመን ወይም ላለመቀበል መጠንቀቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
  • ስለዚህ ወደዚህ ደብዳቤ ለመቅረብ በጣም ጥሩው መንገድ እስካሁን አልተረጋገጠም ማለት ነው። ደብዳቤው እውነት ነው የሚለውን ከመቀበላችን በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ወይም ከሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ኦፊሴላዊ ማረጋገጫ መጠበቅ አለብን።
  • ይህ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ አስፈላጊ ነው ደብዳቤው እውነት ቢመስልም እርግጠኛ ለመሆን ከታመኑ ምንጮች ማስረጃ እንደሚያስፈልገን ያሳያል። መረጃን ያለማስረጃ መቀበል ወይም አለመቀበል ግራ መጋባትና ስህተትን ያስከትላል።

ማጣቀሻዎች

-       https://nbe.gov.et/about-us/governance-of-the-bank/

-       https://www.afis.africa/en/portrait/mamo-e-mihretu/

-       https://addisfortune.news/ethiopias-sovereign-fund-gets-mamo-mihretu-as-founding-ceo/

-       https://borkena.com/2023/01/21/ethiopian-pm-removed-national-bank-governor-appoints-world-bank-man/

-       https://en.wikipedia.org/wiki/Mamo_Mihretu

-       https://www.bbc.com/amharic/articles/cwy8544e1gpo

 

 

 

ጸሃፊ: ነሞምሳ ዋቅቶሌ