post-thumb

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ለአሰብ ጦርነት ውትድርና ተመዝገቡ የሚል መልዕክት በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተላልፏል?

የትምህርት ሚኒስቴር 2017 . 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት  ይፋ ማድረጉን ተከትሎ 22.3 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የዩቲዩብ ገጽ "ለአሰብ ጦርነት ውትድርና ተመዘገቡ ሲል የአብይ ትውልድ ጠል በብርሃኑ  ነጋ አሳውቋል" የሚል መረጃ ተሰራጭቷል። በዚሁ ዓመት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን እንደሚመለከትም ተሰራጭቷል።

ዘገባው ሃሰተኛ መሆኑን ማረጋገጫዎች

የተሳሳተ አኃዛዊ መረጃ ተላልፏል፡፡ በዚህም ከተፈተኑት 3 በመጨመርና ያለፉትን 9 በመቀነስ ገልጿል፡፡ ይህም መረጃው ከታማኝ ምንጭ ላለመወሰዱ ማሳያ ነው።  በትምህርት ሚኒስትሩ / ብርሀኑ ነጋ የተገለጸው ትክክለኛ አሃዛዊ መረጃ 2017 / 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተፈተኑት 585,879 ተማሪዎች እንደሆኑና 50 በመቶ አምጥተው ያለፉት ደግሞ 48,929 ተማሪዎች እንደሆኑ ነው፡፡ 

ይህ ገፅ ከዚህ ቀድሞ ባጋራው መረጃ ለተማሪዎች መውደቅ ተጠያቂው በዋነኝነት የትምህርት አስተዳደር አካላት እንደሆኑና የወደቁት እጣፈንታ እንደሌሎች ታፍሰው ወደ ጦር ማሰልጠኛ ይገቡ ይሆን የሚል መረጃን አስተላልፏል።

ካለፉት አራት አመታት በብዛት ከፍ ያለ ተማሪ ያለፈው 2017 . ነው። 2014 3.3% 2015 3.2%  እና 2016 ደግሞ 5.4% ተማሪዎች ብቻ ነበር ያለፉት። 2017 ግን 8.4% ነው፡፡ ይህም መንግስት  የትምህርት ጥራትን ማሻሻል በሚል ከአመታት በፊት ጀምሮ የሚከተለው ፖሊሲ እንጂ ከባህር በር ጥያቄና ለአሰብ ጦርነት ውትድርና ምዝገባ ከሚለው መረጃ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፡፡ በተጨማሪ ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ አመትም የማካካሻ ትምህርት/ሪሚዲያል እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ ይህም የወደቁ ተማሪዎችን ለባህር በር ጦርነት ውትድርና ምዝገባ ለሚለው መረጃ ሐሰተኛ ለመሆኑ አንድ ማሳያ ነው፡፡

 ምንም እንኳን እያንዳንዱ ወታደራዊ ተግባርና እንቅስቃሴ ለሕዝብ ይፋ ባይሆንም ማን፣መቼና ለምን መሰልጠን የሚሉት ግን ብዙ ጊዜ ከሕዝብ የተደበቁ አይደሉም። ከዚህ ጋር ተያይዞም ሰሞኑን እየታፈሱ ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ማሰልጠኛ ይወሰዳሉ የሚል መረጃ ታማኝና ገለልተኛ በሆኑ ምንጮች አልተሰራጨም፡፡ 

ምስል: ኢትዮጵያ የባህር በር ስለምታገኝበት መንገድ የተሰጠ ገለፃ

 

ባህር በር የማግኘት ጥያቄ የሚመለሰው በጦርነት እንዳልሆነ ጥያቄው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተገለጸበት ጊዜ እስካሁን ከላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(/) እስከ ታችኛው የስልጣን እርከን ያሉ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡ ይህም ለአሰብ ጦርነት የውትድርና ምዝገባ የሚለው መረጃ ሐሰተኛ ስለመሆኑ ሌለኛው ማስረጃ ነው። 

ምሁራንና ፖለቲከኞች 12 ክፍልን ብሔራዊ ፈተና ውጤት አንድምታ እንደምልከታቸው ያስቀመጡ ሲሆን  ማናቸውም የባሕር በር ጥያቄን ለመፍታት ከሚተገበሩ እንቅስቃሴዎች ጋር አላገናኙትም፡፡ ይህም ከላይ የተገለጸው መረጃ ሐሰተኛ ስለመሆኑ ሌላው ማስረጃ ነው፡፡

ይህ መረጃ በሰፊው ትንተና ተሰጥቶት የተሰራው ዘገባ ደግሞ የተሰራጨው ትናንትና 1.26 ሚሊዮን ተከታዮች  ባሉት የዩቲዩብ ገጽ ነው፡፡ ትንተናው አጠቃላይ ትችት የበዛበትና (Hasty Generalization) የተዋቀረ እንጂ በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፈ አይደለም።  ማሳያዎቹም   የትምህርት ሚኒስቴር የወደቁትን ተማሪዎች በሙሉ ለመከላከያ ሰራዊት ስልጠና አስተላለፈ በማለት ይገልጻል፡፡ ይህም   በትንሹ የሪሚዲያል ተማሪዎችን አላካተተም ማስረጃዎች ካለመቀመጣቸውም በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት የሚመለምለው 12 ክፍል የወደቁትን ብቻ በማስመሰል እና ከዩኒቨርሲቲና ከመከላከያ ማሰልጠኛ የሚመረቁትን ቁጥር በማወዳደር የመንግስት ትኩረት ውትድርና እንደሆነ ይገልጻል፡፡ 

በአጠቃላይ 12 ክፍል የወደቁ ተማሪዎች ለአሰብ ጦርነት የውትድርና ምዝገባ የሚለውን መረጃ ያሰራጨው አካል የትምህርት ሚኒስትሩን ስም በመጠቀም፣ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሳበውን 12 ክፍል ውጤት እና የሀገሪቱን የባህር በር ፍላጎት በማገናኘት ውዥንብር ለመፍጠር ሞክሯል። ስለሆነም፣ ይህ መረጃ የሰዎች ስነ ልቦና በተለይም ደግሞ ልጆቻቸው የወደቁባቸው ላይ ከባድ አሉታዊ ተጸእኖ የሚያሳድር ሐሰተኛ መረጃ አሰራጭቷል።

ፀሃፊ: ደሳለው ጋሻየ