ለአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሃውልት እየተሰራ ነው?

የተያያዘው ምስል በብዙ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ በብዛት ሲሰራጭ በ facebook ብዙ እይታዎችን ማትረፍ ችሏል ። ይህንን ተከትሎ የ ሃጂ አወል አርባ ወዳጆች እና አድናቂዎች ድጋፋቸውንን እና አድናቆታቸውን ሲገልጹ አንዳንዶቹ ይህ ሃውልት የ አፋር ህዝብ ንብረቴ ነው ብሎ በሚቆጥራት የአሰብ ከተማ አደባባይ ላይ እየተሰራ ነው የሚሉም አልጠፉም።
መረጃው ምን ያህል እውነት ነው?
ምስሉ እና ምስሉ ያካተታቸውን ነገሮች በመመልከት ይህ ሃውልት አፋር ክልል ውስጥ እንዳልሆነ በ ግልጽ ይታያል። ምስሉን በጥንቃቄ በምንመለከትበት ጊዜ ብዙ የሚያጠራጥሩ ነገሮችን ልናገኝ ችለናል።
በመጀመሪያ በምስሉ ውስጥ የሌላ ሃገር ቋንቋ የተጻፈባቸው ባነሮች አሉ። በቀይ የተጻፈው ባነር በ Telugu ወይም የ ድራቪያን ቋንቋ በመባል በሚታወቀው ደቡባዊ ህንድ ቋንቋ እንደተጻፈ ያመላክታል።
ሲቀጥል ይህ አደባባይ ትክክለኛ ስፍራ የት ነው የሚለውን ስናጣራ ምስሉ የሚገኘው በ ደቡብ ህንድ ውስጥ አንድራ ፕራዴሽ በምትባል ከተማ ውስጥ እንደሆነ ልናረጋግጥ ችለናል።
ሃውልቱ የተሰራው በ አንድራ ፓራዴሽ በምትባል ከተማ ውስጥ ሲሆን ሃውልቱ የተሰራውም ለቀድሞው የከተማዋ ሚኒስቴር Y.S Rajasekhara reddy እንደሆነ ተረጋግጧል።
የምርምራ ሂደቶች ይህ የአፋር ክልል ፕርዚደንት ሃውልት ነው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ምስል ትክክለኛ እንዳልሆነ እና በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተቀነባበረ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል።