post-thumb

የግብፁ አምባሳደር በኤርትራ በኩል አድርገው መቐለ ገብተዋል?

በማህበራዊ ሚዲያዎች የግብፅ አምባሳደር በኤርትራ አድርገው ወደ መቐለ ገቡ የሚል የውሽት መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል። ይህን  መረጃ እና ቪዲዮ ካጋሩ የፈስቡክ ገጾች መካከል wasu mohammed reju የተባለ ከ84 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘Triangle of Afar’ የሚል ስም ያለው ከ265 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሏቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ይገኙበታል ። ገፆቹ ህንዳዊ የህክምና ባለሙያን የግብፅ አምባሳደር እንደሆነ አድርገው አቅርበውታል።

በነዚህ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች የተጋራው መረጃ ቪዲዮው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የሆኑት ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፤ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ እና ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ከሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር በተጨማሪ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከአንድ የህንድ የህክምና ባለሙያ ጋር ሲወያዩ ይሳያል ።

ይህ በ‘Triangle of Afar’ የፌስቡክ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የተጋራው ቪዲዮ ከ870 ሺህ በላይ እይታ ያገኘ ሲሆን ከ600 የሚልቁ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ  መረጃዉን ለሌሎች አጋርተዉታል።(https://www.facebook.com/share/r/14PLpH4kB83/)

ከትግራይ ክልል እና ህወሓት አመራሮች ጋር ሲነጋገር የሚታየው ግለሰብ የህንድ ሀገር ዜጋ ሲሆን ቪዲዮው የተቀረጸዉም ከአንድ ወር በፊት በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ተዋጊዎች የህክምና አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ መሆኑን የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምጺ ወያነ የተባሉ ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ሚዲያዎች ዘግበውት ነበር ።

ይህንን መረጃ እና የህክምና ባለሙያው ከህንድ አገር እንደመጡ የሚያውቁ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የወጣው መረጃ ስህተት እንደሆነ እና የግብጽ አምባሳደር ሳይሆን የህንድ የህክምና ባለሙያ እንደሆነ ገልጸው ነበር።

በወቅቱ  ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ካጋለጡት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መካከል Tigrai online እና ሳባያን ሚድያ የሚባሉት እና ሌሎች ይገኙበታል። (https://www.facebook.com/100064877674649/posts/pfbid02MF7SZBbzjeyNiff63JhP2pmkWsEVZK3hhStsd5peRkEWoiuejYTSnF8MTEAB4pb3l/?app=fbl) እና

https://www.facebook.com/100090996107827/posts/pfbid0zR92ni7wt3GzrsqrhSSqs1MXPy4u79iDE7JGkJDByCMFF9LQVviA8CsCp3zDVH9Pl/?app=fbl)

አሁን በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚስተዋለዉ ትልቁ ችግር መረጃዎች ሳያጠሩ በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራት ሲሆን ሁሉም መረጃን አጣርቶ በማጋራት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።

ፀሃፊ: ፊሊሞን ደስታ