post-thumb

የኢትዮጵያና ኤርትራን ውጥረት ተከትሎ የተሰራጩ አሳሳች ምስሎች

ከጊዜ ወደ ጊዜ የተዛቡና ሀሰተኛ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያ (ቴሌግራም፣ፌስቡክና ቲክቶክ )በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛሉ።በተለይም በግጭት ወቅት የሀሰት መረጃዎች በሰላም፣ በብሔራዊ ደኅንነትና በኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላሉ።


በቀን 18-02-2018 አ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በስድስተኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በተናገሩት ንግግር “ማንም ፈለገም አልፈለገም ኢትዮጵያ ተዘግታ አትኖርም” በማለት የኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎት ማለትም የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ቀይ ባህር ሉዓላዊ መዳረሻ የማግኘት ፍላጎት በኤርትራ መንግሥት ዘንድ እንደ ጦርነት ማስፈራሪያ ተደርጎ መታየቱ ዋናው አለመግባባት ሆኗል።
በዚህም የተነሳ ብዙ ሆን ተብለው የሀሰት መረጃዎች (misinformation) እና የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ፈጠራ የሆኑ ቪዲዮዎች እና ፎቶግራፎች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በፌስቡክ  ፣ቲክቶክ እና ኤከስ ላይ በስፋት ሲስፋፉ ይገኛል። በተለይም የፖለቲካ ውጥረት በሚኖርበት ጊዜ በተደጋጋሚ የሚታዩት የሀሰት መረጃዎች በህብረተሰቡ ሉአላዊነት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እያመጣ ይገኛል።

የተሳሳተ መረጃ እና የሀሰት ዜና ብዙውን ጊዜ የሚሰራጨው ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ሀብት መሆኑን ለማሳየት  ያደረገችውን   አቋም በተመለከተ  ሲሆን ይህም የቀጣናዊ ውጥረቶችን ለማባባስ አስተዋፅኦ ያደርጋል። እነዚህ ከታች የምናያቸው በአብዛኛው የሚያካትቱት በኤአይ የተፈጠሩ ፕሮፓጋንዳዎችን፣ የሀሰት ወታደራዊ እርምጃ  ውንጀላዎችን እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረጉ የተሳሳተ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻዎችን ነው።ከነዚህም ውስጥ ይህ የፌስቡክ ምስል ተጠቃሽ ነው።

ለምሳሌ ይህ ምስል በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው አለመግባባት  በኢትዮጵያ ወታደሮች አሰብን ለማስመለስ የጦርነት ዘመቻ እየተሰሩ መሆኑን እና  ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መዋጋት  ጀምረዋል የሚሉ መረጃዎችን ሲገልፅ መረጃውን ያጋራው "Ethio Media" የተሰኘ ገጽ ነው።

"BREAKING NEWS"  የሚለው ጽሑፍ በቪዲዮው ላይ የተቀመጠበት መንገድ ብዙ ጊዜ ትኩረት ለመሳብ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮዎች ላይ የሚደረግ የፕሮፓጋንዳ ወይም ጠቅ የማስደረጊያ (Clickbait) ዘዴ ነው። በተጨማሪም  የቪዲዮው መከፋፈል ዋናው ክስተት በአንድ ቪዲዮ መቅረብ ሲገባው፣ ይህ ምስል በአንድ ገጽ ላይ ሶስት የተለያዩ ተያያዥነት የሌላቸውን ወታደራዊ ምስሎች አንድ ላይ አድርጎ ያሳየናል። ይህ በራሱ ለማሳመን ወይም ከፍተኛ ድንጋጤ ለመፍጠር ተብሎ የተሰራ መሆኑን ያመለክታል።

የሄሊኮፕተሩ ምስል በጣም ከፍተኛ ጥራት (High-Resolution) ያለውና ሰው ሠራሽ (Synthetic) የሚመስል ነው።

የብርሃን አቀማመጡ (Lighting) እና ጥላው (Shadows) በጣም ስለታም እና ከእውነታው የራቀ ይመስላል ይህም ከቪዲዮ ጌም (Video Game) ወይም ከ CGI/AI ሞዴሊንግ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል። ስለዚህ ይህ ምስል እውነት የመሆኑ ዕድል በጣም ዝቅተኛ ነው።   ከዚህም በተመሳሳይ  ይህ ቅጂ ተጠቃሽ ነው(https://www.facebook.com/share/r/1Ft3D3dQaX/)

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ይህ መረጃ ሀሰት ነው እንድንል የሚያሰገድዱ ምክንያቶች አሉ።  ኢትዮጵያ የትኛውንም አይነት ጦርነት እንዳወጀች የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ አለመኖሩ በተጨማሪም የሀገር ጉዳይ እንደመሆኑ  በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች መዘገብ አለመቻሉ በተጨማሪም በታማኝ ምንጮች ለምሳሌ  ይህን ክስተት በEBC፣ አልጀዚራ፣ ቲክቫህ ወይም በሌሎች ታማኝ የዜና ምንጮች ምን አሉ ሚለውን በሚጣራበት ጊዜ በጊዜው ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ አለመሰጠቱን ተመልክተናል ።  እነዚህ ምስሎችና ቅጂዎች በAI የተሰሩ መሆናቸውን ያጣራንበት መንገድ  (Tools & Technical Methods) የምስል ምንጭ መፈለጊያ (Reverse Image Search) ተጠቃሽ ነው።

እንደዚህ አይነት መረጃዎች ሲገጥሙን ከማጋራታችን በፊት የምንጩን ታማኝነት ማረጋገጥ ማለትም  መረጃው የመጣው   ከታማኝ የዜና ገፅ መሆኑን ማረጋገጥ እና ይህን መሰል በAI የተሰሩ ምስሎችን ለማጣራት ለምሳሌ  ያልተለመደ ብርሃን፣ የተዛቡ ጽሑፎች  ወይም ከመጠን በላይ የድምፅ መቆራረጥ ተጠቃሽ ሲሆኑ  የምስሉን ምንጭ ስንፈልግ ምስሉን በመጠቀም Reverse Image Search (እንደ Google Lens) በመጠቀም  መረጃው ከሌላ ክስተት ላይ  የመጣ ወይም  ወይም የቆየ ዜና መሆኑን ፣ እንደ TinEye  ያሉትን በመጠቀም ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የት ቦታ እንደታተመ እና በኢንተርኔት ላይ በሌላ መልኩ ተቀይሮ ወይም ተቆራርጦ (Edited or Cropped) እንደሆነ ማወቅ ያስችለናል። 

በተጨማሪም ከመጠን በላይ ስሜት ቀስቃሽ ወይም ድንጋጤ የሚፈጥር መረጃ ከሆነም ወዲያውኑ ከማመን እና ቶሎ ከማጋራት ይልቅ የተለያዩ ማጣሪያ ድረ-ገጾችን ተጠቅሞ እውነታው ላይ መድረስ ከተለያዩ በሀሰተኛ መረጃዎች ምክንያት የሚመጡትን ችግሮችና አደጋዎች ለመቀነስና ለመፍታት ይጠቅማል።                                             

ፀሃፊ: ሰብለ እሸቱ