የኦንላይን ማጭበርበር በሃገራችን
የኦንላይን ማጭበርበር ማለት አንድን ሰው በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም የሆነ ነገር ቃል በመግባት (ስራ፣ ትምህርት ወ.ዘ.ተ) እነዛን ነገሮች እንደሚያሳኩላቸው በማሳመን ከነዛ ሰዎች ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን እንዲሁም እምነታቸውን ያለ አግባብ የሚቀሙበት ስልት ነው።
የድርጊቱ ፈፃሚዎችና ተጠቂዎች
በብዛት ለነዚህ አይነት ጉዳቶች ተጋላጭ የሚሆኑት ህይወታቸውን ለመለወጥ ደፋ ቀና የሚሉ ቀን ተሌት የሚለፉ ሁሌም ህይወታቸውን ለመለወጥ አቋራጭ መንገድ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። አጭበርባሪዎች ይህንን ስስ ጎናቸውን በመፈለግ በዛ ደካማ ጎናቸው ገብተው እምነታቸውንም እስኪያገኙ ለስለስ ብለው ቀርበው ሚፈልጓትን ካገኙ በኋላ ግን ዞር ብለው አያዩዋቸውም።
እነዚህን የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመተግበር ብዙ አይነት የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ሲጠቀሙ ከነዚህ መካከል ቴሌግራም ዋነኛው ሲሆን ዋትስአፕ እንዲሁም በ ቲክቶክ ወ.ዘ.ተ ተግባራዊ ይደረጋሉ።
ከእንላይን መጭበርበር ጋር በተያያዘ የአንድ ሰው ታሪክ እዚህ ጋር እናምጣ።ተጠቂው “የሆነ የድሮ የሴክሽን ግሩፕ ነበር እና እዛ ላይ የተለቀቀ የድሮ የቴሌግራም ግሩፕ እንደሚገዙ እና የዘረዘሩት ዋጋ በጣም አሪፍ ነበር ገብቼ አወራኋቸው ልጁ ስሙ ‘mohammed buyer‘ ይል ነበር ይህም እንዳምነው አደረገኝ ብዙ ግዜ mohammed የሚባል ሰው አይዋሽም ስለሚባል ወይም ይታመናል ስለሚባል ከዛ owmershipኡን ወደኔ አስተላልፍ አለኝ እኔ የነበረኝ የ 2023 ግሩፕ ነበር ዋጋው በዛ ሰአት 1000 ብር ነበር እሱ ግን ያቀረበልኝ 1700 ብር ነበር። ከዛ አካውንት እንድልክ ነገረኝ ላኩለት ከዛም እንዴት ላምነው እንደምችል ጠየቅኩት እሱም ላምነው እንደምችል እና ከዚህ በፊት የላከላቸውን ሰዎች screenshot ላከልኝ ከዛ 1 ነገር ተጠራጠርኩ screenshotኡ ላይ ላኪውን ያሳያል እና ሁሉም ላይ mohammed የሚል ስም የለም ሌላ ቢሆን እንጂ እውነት ለመናገር ከዛ ውጪ ሌላው ነገር እውነት ይመስል ነበር። ከዛ እንደምንም እየተጠራጠርኩኝም ቢሆን ownershipኡን አስተላለፍኩለት ከዛ ብሩን ካሁን ካሁን ይልካል እያልኩ መጠባበቅ ጀመርኩ ስጠብቅ ስጠብቅ ዝም ነው ደግሞ ብሎክም አላደረገኝም ያ ትንሽ ተስፋ ሰጠኝ ከዛ ጠየቅኩት መች እንደሚያስገባ ከዛ ትንሽ ስራ ስለበዛበት ትንሽ እንደጠብቀው ነገረኝ ከዛም ጠበቅኩ ጠበቅኩ ምንም የለም ከዛ አሁንም ስጠይቀው እሺ ይለኛል በስተመጨረሻ ከ 1 ቀን በኋላ ብሎክ አደረገኝ የቴሌግራም አካውንቱን እና ቻናሉን ሪፖርት አደረግኩበት እና እናንተንም ከንደዚህ አይነት መጭበርበር ይራሳችሁን ጠብቁ ማለት እወዳለሁኝ ” ሲል ሃሳቡን አጋርቶናል።
እንዴት ራሳችንን ከአጭበርባሪዎች እንጠብቅ?
1 ከማናውቃቸው ሰዎች የሚላክልንን ማንኛውንም መልእክትም ሆነ ሊንክ ሳናረጋግጥ አለመንካት
2 ሁሌ አቋራጭ መንገዶችን መፈለግ ማቆም
ፀሃፊ: አብዱ