post-thumb

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትና የማታለያ መንገዶቹ

ሃገራችን ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሀገር ለመሆን ጥረት እያደረገች  ብትሆንም በስራ ስምሪት ዘርፉ ሰፊ ክፍተት እያታየ እና ህጋዊ እርምጃ ባለ መወሰዱ ህገ ወጥ ደላሎች እየተበራከቱ መጥተዋል ።

ህጋዊ መሠረትም ሆነ ከውጭ ሀገራት ጋር ውል ሳይኖራቸው ‘ወደ ውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት እንሰጣለን’ እያሉ በሚያጭበረብሩ አካላት እንዳይታለሉ፣  ዜጎች ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡት ቢገኝም አሁንም በርካቶች አየታለሉ ይገኛሉ።

የውጭ ሀገራት ሥራ ስምሪት የሚሰጠው በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካኝነት ብቻ መሆኑ ሲታወቅ ዜ ጎች ካሉበት ሆነው ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት መመዝገብ የሚችሉበት የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በማመቻቸት(  https://lmis.gov.et/) ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም ።

በማህበራዊ ሚዲያም በርካቶች የተሳሳተ መረጃ በማስተላለፍ  በተለይም ለወጣቶች ስራ እናሰማራለን በሚል የማይጨበጥ ተስፋ በመሰጠት ህይወታቸውን  እና ገንዘባቸውን አደጋ ላይ ይጥላሉ።

ይህንን የማታለያ ዘዴ በመጠቀምም  ሃገራችን ህጋዊ ማዕቀፎች ወ ደፈረመችባቸው ሥድስት የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ለመሄድ የሚፈልጉ በሕጋዊ መንገድ እንልካለን እያሉ እያሰራጩ ይገኛሉ ።

በቅርቡ በእንዲህ አይነት መታለያ ዘዴዎች እና በህገ ወጥ መንገድ  ተታለው ወደ ውጭ አገራት ለመሄድ ከትግራይ ክልል ተነስተው በአፋር አድርገው ወደ ተለያዩ ሀገራት ሊሄዱ የነበሩ 106 ሰዎች በጥቅምት ወር በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ተመልሰዋል።

https://www.facebook.com/61553650610361/posts/pfbid0cFRCcCZErkuf4NSUchq2Ly8GHUbqTTbmwvQjL1gtRbQVVnEYGxXzh3LwP5a2eGQ5l/?app=fbl

https://www.facebook.com/100068990923111/posts/pfbid02mYUfE7PY25DsNFAupXVFNjvVttpJkFZhhtMpHXPxe7hTwZ1Ng4uo7jyNAimxoPHol/?app=fbl

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመንግሥት ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ ወደ ውጭ ሀገራት የሚደረግ የሥራ ስምሪት አለመኖሩን በመገንዘብ፤ ዜጎች ሕይወታቸውን፣ ጊዜያቸውን ብሎም ገንዘባቸው ከማጣት እንዲቆጠቡና እራሳቸውን እንዲጠብቁ በተጨማሪ  ህጋዊ እውቅና እንዳላቸው ማረጋገጥም ይገባል።

በሀሰተኛ መረጃ የሰው ሕይወትን እና ንብረት በቀላሉ መንገድ እየጠፋ ሰለሆነ ሀሰተኛ መረጃዎች  በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች ሲሰራጩ በማጣራት እና እውነተኛነቱን በማረጋገጥ እንድንጠቀምበት የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር ግዴታችን ነው።

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ካስፈለገም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤቱ እና ሌሎች ህጋዊ እውቅና በተሰጣቸው ተቋማት አማካኝነት በተዘረጉ አሠራሮች በየወረዳቸው በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ  ማሰልጠኛዎች በመሰልጠን ደህንነታቸው ብሎም ተጠቃሚነታቸው ተጠብቆ ስምሪቱን የሚያገኙበት ሁኔታ እንዳለ መረዳት ይገባል 

ህጋዊ ከውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ጋር በተያያዘ መረጃዎችን ለማግኘት በ9138 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል እውነተኛ መረጃ ማግኘት ይቻላል ።

ፀሃፊ: ፊሊሞን ደስታ